Telegram Group Search
#ይህ ሳምንት ከሰርከ ሆሳዕና እስከ ትንሣኤ ያሉትን ቀናት
ያካትታል::

#የጌታን መከራ እንግልት መሰቀል መሞት መቀበር የምናስብበት ነው:: ለእኛ ሲል የተቀበላቸውን 13ቱ ሕማማተ መስቀል በማሰብ በልቅሶ በስግደት በጸሎት ልናሳልፈው
ይገባል:: በዚህ ሳምንት ሊሰሩ ያልተፈቀዱ በርካታ ናቸው::
በመስቀል መባረክ ማማተብ መሳቅ መሳሳም ከሴት ጋር
መገናኘት ኑዛዜ መፈጸም ፈጽሞ የተከለከለ ሲሆን የ5500ው
የጨለማ ዘመን መታሰቢያ በመሆኑ መንበሩ በጥቁር ልብስ
ይሸፈናል ካሕናትም ጥቁር ይለብሳሉ:: በዚህ ሳምንት ለሞተ
ጸሎተ ፍትሐት አይጸለይለትም ክርስትናም እንዲሁ አይፈጸምም::
እግዚአብሔር ይፍታህ አይባልም ሳምንቱ የሚታሰበው ሕማሙን
ሞቱን በማሰብና በስግደት ነው:: የግዝት በዓላት እንኳ
ይሰገድባቸዋል:: የዚህ ሳምንት ጾም የቻለ ሁለት ሁለት ቀን
ያልቻለ እስከ ጀንበር ግባት ድረስ ነው:: ምግቡም ቆሎ ዳቦ
የላመ የጣመ ያልሆነ ደረቁን በበርበሬ ነው መጠጡም ንጹህ
ውኃ ነው:: ጠጅ ያንቆረቆረ ጮማ የቆረጠ እድል ፈንታው ጽዋእ
ተርታው በጌታ ሞት ከተደሰቱት ከአይሁድ ጋር ነው:: ጸሎቱ
ውዳሴማ ርያም አንቀጸ ብርሃን መልክአ ሕማማት መዝሙረ
ዳዊት ነው:: የቅዱሳን መልክአ መልክእ አይጸለይም:: የጾሙ
ሥርዓት ምን ይመስላል ካሉ፡
ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15

ቁጥር 578፡ በሊህ በስድስቱ ቀኖች (በሰሙነ ሕማማት) ከቂጣ
ከጨው ከውኃ ብቻ በቀር አይብሉባቸው፡፡ በሊህ ቀኖች ከወይን
ከሥጋ ተለዩ የኀዘን ቀኖች ናቸውና የደስታ ቀኖች አይደሉም፡፡
ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ጹሟቸው፡፡ የሚችል
እስከ ሌሊቱ ዶሮ ጩኸት ጊዜ ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው
ሰውየውም ሁለቱን ቀኖች በአንድነት መጾም ባይቻለው ግን
የቅዳሜን ጾም ይጹም፡፡

ቁጥር 590፡ ካህን ሰሙነ ሕማማትን ቀንና ሌሊቱን ሳያስተካክል
አስቀድሞ ቢያውል ይሻር፡፡ ከሕማማት ቀጥላ ከምትሆን ከቅዳሜ
ስዑር በቀር እሑድንና ቅዳሜን የጾመ ካህን ቢኖር ይሻር፡፡

ቁጥር፡ 593፡ ከካህናት ወገን ማንም ቢሆን በአርባ ጾም
በዓርብና በረቡዕም ጾም ወይን መጠጣት አይገባውም ወደ
መዋት (ውሽባ ቤት) አይግባ፡፡ በዐቢይ ጾም ወራት ሰው ከሚስቱ
ጋር አይተኛ፡፡

ቁጥር 597፡ ሴቶችም ጌጣቸውን ይተው፡፡ ሁሉም ለእያንዳንዱ
በአርባ ጾምና በሰሙነ ሕማማት መጠበቅ ይገባዋል ድኅነታችንና
የኃጢአታችን ሥርየት በእነርሱ ነውና፡፡ ይኸውም ሥራ አንዱስ
እንኳ በአርባ ጾም ወራት በምንጣፍ ፈጽሞ እንዳይገናኝ ከጋብቻ
ሕግ የወጣ ነው፡፡ ክብርት በምትሆን በሕማማት ወራት ይህችን
ኃጢአት የሚሠራት ሰው ወዮለት፡፡ በአርባ ጾም በተድላ በደስታ
ፈቃዳችንን ካደረግን ትንሣኤውን ባየን ጊዜ ተድላ ደስታችን
ወዴት አለ?

ቁጥር 599፡ በተባሕትዎ በትሕትና አርባ ቀን ጾምን ይጹሙ፡፡
ከጥሉላት መከልከል ይገባል፡፡ አያግቡም፡፡

ቁጥር 600፡ በሰሙነ ሕማማት ክርስትና ማንሣት ክህነት
መስጠት ለሞቱ ሰዎች መጸለይ አይገባም፡፡ በእነዚህም ቀኖች
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፈጽሞ ማገልገል ይገባል እንጅ፡፡
በሰሙነ ሕማማት ስለሚሞቱት ሰዎች የሙታን ግንዘትና
የሐዋርያት ሥራ ወንጌላት የሙታን ፍትሐት በሆሣዕና በዓል ቀን
ይነበብ እንጅ፡፡

ቁጥር 601፡ በጸሎተ ሐሙስ ጸሎተ ተአምኆ እግዚአ ሕያዋን
የቡራኬ ጸሎት አይባልም (አይጸለይም)፡፡ ቅዳሜ ግን እግዚአ
ሕያዋን ይባላል ፍትሐት ይፈታል፡፡ ከመሳለም በቀር ጸሎተ
ዕጣንም ይጸለያል፡፡ በዕለተ እሑድ ግንዘት ማድረግ በፋሲካ
ቀንም ማልቀስ አይገባም፡፡ ዳግመኛም በውስጧ በአርባ ጾም
ከተድላ ከደስታ ወገን ምንም ማድረግ አይገባም፡፡ መጋባት
ክህነት መስጠት ክርስትና ማንሣት ከሹመትም ወገን
ስለሚሞቱት ከመጸለይ በቀር ምንም ማድረግ አይገባም፡፡
ይሞታል ተብሎ ለሚያስፈራው ግን ጥምቀተ ክርስትና
ይደረግለታል፡፡
የተከለከሉ ነገሮች ምን ምን ናቸው ካሉ፡
1. እጅ ተጨባብጦ ሰላምታ መባባል መሳሳም
2. ሩካቤ ሥጋ ማድረግ
3. መስቀል ማሳለም እና መሳለም
4. ክርስትና ማስነሣት
5. ለሙታን ፍትሐት ማድረግ
6. ክህነት መስጠት
7. የላመ የጣመ ምግብ መመገብ
8. መሳቅ መጫዎት መጨፈር
9. አብዝቶ ጠግቦ መመገብ
10. መስከር ወዘተ ናቸው፡፡


https://www.tg-me.com/ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ/com.ortodoxtewahedo
#ሕማማት መስቀል " ተብለው የሚዘከሩት አሥራ ሦስት ሲሆኑ እነዚህም፦

1. በብረት ሐብለ መጋፊያና መጋፊያው እስኪጋጠም ድረስ የኋሊት መታሰሩ

2. ከአፍንጫው ደም እስኪውጣ ድረስ 25 ጊዜ በጡጫ መመታቱ

3. 65 ጊዜ ከግንድ ማጋጨታቸው

4. 120 ጊዜ በድንጋይ ፊቱን መመታቱ

5. 365 ጊዜ በሽመል መደብደቡ

6. 80 ጊዜ ጽህሙን መነጨቱ

7. 6666 ጊዜ መገረፉ

8. አክሊለ ሦክ በራሱ ላይ መደፋቱ

9. 136 ጊዜ በምድር ላይ መውደቁ

10. ሳዶር፡ አላዶር፡ ኤዴራ፡ ዳናትና ሮዳስ በሚባሉ 5ቱ ቅንዋተ መስቀልበችንካር መቸንከሩ

11. መራራ ሐሞትን መጠጣቱ

12. መስቀሉን ተሸክሞ መንገላታቱ

13. በመስቀል መሰቀሉ ናቸው።

https://www.tg-me.com/ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ/com.ortodoxtewahedo
#ቤተ_ክርስቲያን_መሄድ_ለማትችሉ_ሰሙነ_ሕማማትን_በስደት_በሥራ_ለምታሳልፉ_በየቤታችሁ_ሁናችሁ_ለምትሰግዱ_እንዲህ_እያላችሁ_ስገዱ 🙏

👉በመጀመሪያ በስመአብ ብለን የዘወትር ጸሎትን አድርሰን ውዳሴ ማርያምን ቆመን እንደግማለን

በመቀጠል

👉 ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም

👉 አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከለዓለመ ዓለም

👉 ኦእግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከለዓለመ ዓለም

👉 ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኮቴት

🙏 አቡነ ዘበሰማያት / አባታችን ሆይ/

ከቻልን እየመላለስን 12 ግዜ እያልን መስገድ 12 ጊዜ ካልቻልን የቻልነውን ያህል

👇 ይህን ስንጨርስ በዛው ቀጥለን

🙏 ለአምላክ ይደሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም

🙏 ለስሉስ ይደሉ ክብር

🙏 ለማኅየዊ ይደሉ ክብር

🙏 ለእዘዙ ይደሉ ክብር

🙏 ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር

🙏 ለሥልጣኑ ይደሉ ክብር

🙏 ለምኩናኑ ይደሉ ክብር

🙏 ለኢየሱስ ይደሉ ክብር

🙏 ለክርስቶስ ይደሉ ክብር

🙏 ለሕማሙ ይደሉ ክብር

👉 እስከ አርብ ድረስ እስከዚህ ሲሆን አርብ ለመስቀሉ ይደሉ ይጨምራል

እንዲህ እያልን ከሰገድን በኋላ መዝሙረ ዳዊትን መጽሐፍ ቅዱስ ከኦሪት ከነቢያት ከወንጌል የቻልነውን እናነባለን

ከዛም 👇

👉 ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን ኪርያ ላይሶን

👉 ክርያላይሶን ኪርያላይሶን ዕብኖዲ ናይን ኪርያላስይሶን

🙌 ታኦስ

🙌 ማስያስ

🙌 ኢየሱስ

🙌 ክርስቶስ

🙌 አማኑኤል

🙌 ትስቡጣ

👇 እንዲህ እያልን ከሰገድን በኋላ

41 ጊዜ የቻለ ከዛም በላይ ኪርያላይሶን እያሉ መስገድ ነው።

የቃላት ትርጉም

👉 ኪርያላይሶን ማለት ቃሉ ግሪከኛ ሲሆን አቤቱ ማረን ማለት ነው

👉 ዕብኖዲ ማለት የግጽ ቅብጥኛ ሲሆን አምላክ ማለት ነው

👉 ናይን /ናይናን/ ማለት እኛን ማረን / ቅብጥኛ/

👉 ታኦስ / ግሪከኛ / አምላክ

👉 ማስያስ ።/ እብርይስጥኛ / መሲሕ

👉 ኢየሱስ መድኃኒት

👉 ክርስቶስ ንጉሥ ቅቡዕ የባሕርይ አምላክ

👉 ትስቡጣ /ግሪክኛ / ደግ ገዥ

🤝 የቃሉን ትርጉም እንዲህ እያሰብንና እየተረዳን መስገድ ይገባናል ።ላስተማሩን አባቶቻችን ቃለ ህይወት ያሰማልን።

https://www.tg-me.com/ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ/com.ortodoxtewahedo
#ሰሙነ ሕማማት (ዘሰሉስ)
ማክሰኞ

#የጥያቄ ቀን በመባል ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ምክንያት በዚህ ዕለት ስለ ሥልጣኑ በጻሕፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፡፡

ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተአምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታት በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? የሚል ነበር ይህንስ ሥልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች? ከሰማይ ወይስ ከሰው? አላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ነው ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም?
ይለናል፡፡

ከሰው ነው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፤ እንደ መምህርነቱም ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ እኔም አልነግራችሁም አላቸው፡፡

ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተውት አልነበረም፡፡

https://www.tg-me.com/ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ/com.ortodoxtewahedo
እንበለ ደዌ ወሕማም
እንበለ ፃማ ወድካም
አመ ከመ ዮም
ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ
እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም!

"ያለ ደዌና ያለ ሕማም፥ ያለ ፃማና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰን ያድርሳችሁ!"

አሜን!

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo
"ድንግል ሆይ አንቺን የሰደበ ሰው እንዴት ይኖራል " አይኖርም እንጂ ምክንያቱም በልጅሽ የፍርድ መፅሐፍ ላይ እናት አባቱን የሰደበ ሰው ይሙት ይላል የጌታን እናት ሰድቦ እንዴት ይኖራል።

#አባ ፅጌ ድንግል

@ortodoxtewahedo
"ይህቺ ጥፊ የኔ ናት"

መነኮስ አባ አርሳንዮስ በገባበት ገዳም ዉስጥ፣ እግዚአብሔርን
እያገለገለ ሲኖር አንድ ቀን ከገዳሙ ሕግ ዉጭ የሆነ ነገር
ይፈጽማል፡፡ ጥፋቱ ከገዳሙ አበምኔት ይደርስና አበምኔቱ አስበዉ
ብገስጸዉ ያፍራል፣ ዝም ብል ጥፋቱ ጥፋት ሳይመስለዉ ሊቀር ነዉ
አሉና፡፡ የሱን ረድዕ ጠርተዉ እንዲህ አሉት፡፡ "አርሳንዮስ ያጠፋዉን
ጥፋት እኔ እያየሁህ በእርሱ ፊት አንተ አጥፋ ከዛ በጥፊ
እመታሃለሁ፡፡ ያኔ እርሱ በአንተ ጥፊ ይማራል አሉት፡፡"
እንደተመካከሩት በአርሳንዮስ ፊት ረድኡ የእርሱን ጥፋት አጠፋ
አበምኔቱም ተቆጥተዉ በጥፊ መቱት በዚህ ጊዜ ነገሩን የተከታተለዉ
አርሳንዮስም "ይህች ጥፊ የኔ ናት" ብሎ ተናገረ፡፡
እግዚአብሔር እኛን ባጠፋነዉ ቅጣት የግድ እስከሚቀጣን ቁጭ
ብለን መጠበቅ የለብንም ፣ከሌላዉ ጥፋት፣ ከሌላዉ ቅጣት መማር
አለብን፡፡ ከሌላዉ ጥፋት መማር ትልቅ ዕዉቀት፣ ታላቅ ማስተዋል
ነዉ፡፡ አርሳንዮስ ጓደኛዉ በጥፊ ሲመታ፣ ይች ጥፊ የኔ ናት አለ እንጂ
ባጠፋዉ ጥፋት ነዉ የተቀጣዉ ብሎ አልፈረደበትም፡፡ እኛም ቁጣ፣
መቅሰፍት፣ እኛ ጋር እስኪመጣ መጠበቅ የለብንም ከጓደኞቻችን
ከጎረቤቶቻችን በሌላም ሀገር ከምናየዉ ከምንሰማዉ ተምረን ንስሓ
መግባት አለብን ጾም ማለትም ይህ ነዉ፡፡ ንስሐ የምንገባዉም
ኃጢአታችንን ስናስተዉል ነዉ፡፡ ማስተዋል ከሌለን ኃጢአቱን እንደ
ጽድቅ ቆጥረን ለንስሐ አንበቃም፡፡
ማስተዋልን ገንዘብ ያደረገ ምዕመን በሌላ ላይ የተደረገ ቅጣት
በርሱ ላይ እንደመጣ ይጠነቀቃል፡፡ እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ
ብልህ በመሆን የነገሮችን ሁኔታ በማስተዋል ይከታተላል፡፡ ከሰብአ
ትካት ከሰዶም ይማራል ሎጥ የዳነበትን መንገድ ይከተላል ቃሉን
በመስማት በኖህ መርከብ በተመሰለች ቅድስት ቤተክርስቲያን
ይገኛል እራሱን በንስሐ በሥጋ ወደሙ በጸሎት በእግዚአብሔር
ቸርነት ከሚመጣዉ መቅሰፍት ያድናል፡፡
የአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን አሜን፡፡

👉 @ortodoxtewahedo
#የሰሙነ_ሕማማት_ረቡዕ

#ምክረ_አይሁድ_ይባላል
ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማቴ. 26÷1-14፣ ማር. 14÷1-2፣ ሉቃ. 22÷1-6) የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡

#የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል
ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለሽቱዋ ማርያም) "ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ" ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ረቡዕ የመዓዛ ቀን ይባላል፡፡

#የእንባ_ቀንም_ይባላል
ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና። (ማቴ. 26÷6-13፣ ማር. 14÷9፣ ዮሐ. 12÷8) ኃጢአትን በማሰብ ማልቀስና ራስን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ከምታስተምረን ማርያም እንተ እፍረት እንባን ለንስሐ ሕይወት ልንጠቀምበት ይገባል፡፡

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻማ ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤሁ በፍስሐ ወበሰላም።

http://www.tg-me.com/ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ/com.ortodoxtewahedo
"#ራስህን ፈልገው "

ወዳጄ ሆይ እባክህን ጌታችን ከተያዘበት ሐሙስ ማታ እስከ ተቀበረበት ዓርብ ያለው ክስተት ውስጥ ራስህን ፈልገው፡፡

በዚያ ከነበሩት ሰዎች አንተ ማንን ትመስላለ?

ወዳጅ አየመሰለ የሚሸጠው ይሁዳ አንተ ነህ?

ወይንስ ፈርቶ የሚክደውን ጴጥሮስን? የአንተ ጠባይ በእነዚያ ሃያ ሰዓታት ውስጥ ከነበሩት ሰዎች ማንን ይመስላል?

ጌታን አስረው እያዳፉ የወሰዱትን ትመስላለህ? በሐሰት የሚመሰክሩበት ውስጥ ነህ?

ወይንስ ያለ ጥፋቱ አስረው ከሚያንገላቱት ውስጥ ነህ?

ያለ ህግ አግባብ በግፍ ከፈረዱበት ውስጥ ነህ? ወይስ ገዢዎችን ለማስደሰት ብለው በጥፊ ከሚመቱት ውስጥ ነህ? እንደ ጲላጦስ አይነት ዳኛ ትሆን?

ንጹሕ መሆኑን እያወቅህ ገርፈኸው ይሆን? ይሰቀል ሲባል አብረው ከሚጮኹት ትሆን? ከሄሮድስ ጭፍሮች ጋር ስቀህበታል ወይንስ ከገሊላ ሴቶች ጋርአልቀስህለታል?

ወዳጄ ሆይ በዕለተ ዓርብ ከነበሩት አንተ ማንን ትመስላለህ?

የቀኙ ወንበዴ ነህ ወይንስ የግራው ፣ የቆምከው ከሰደቡት ጋር ነው ወይንስ ከእናቱ ጋር?

#ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሕማማት መጽሐፍ የተወሰደ

#ለመቀላቀል

👉 @ortodoxtewahedo
Audio
ሕማማት

 "በሕማማት የሚደረጉና የማይደረጉ ነገሮች"          
                          
Size:- 26MB
Length:-1:14:43
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@ortodoxtewahedo
   "ጌታዬ እጠበኝ"
እግሮቼ የዛሉ ብዙ የተጓዝኩኝ
በቀኝ በግራ ስል መድረሻ ያጣሁኝ
ከጠባቧ መንገድ መርጬ ሰፊውን
በሰፊው ጎዳና ላይ እታች ስኳትን
ንጽሐ ሰውነቴን በበደል ያቆሸኩ
ንጽሐ ልቦናዬን በክፋት ያሳደፍኩ
በኃጥያት ቀንበር ሸክሜ ያጎበጠኝ
ውስጤ ክፋት ሞልቶት ጉልበቴ የከዳኝ
በነፍስ በስጋዬም እጅግ ደካማ ነኝ
ምህረትን የምሻ ተግባር የጎደለኝ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ልክ እንደ መጻጉ እንደ ምስኪኑ ሰው
ባህር ውስጥ ሚከተው ዘመድ እንደሌለው
መዳንን ትሻለክ ብለክ የጠየከው
በባህር ውስጥ ሚከት የለኝም መልካም ሰው
ብሎ እንደመለሰው
አይደለሁም እኔ አልጋ ላይ የቀረው
አካሌ የከዳኝ የቆምኩ የመሰለኝ
አልጋህን ተሸክመህ ሂድም እንዳትለኝ
በኃጢያት በሽታ መታመሜን ማላምን
መድኅኒት እንዳላገኝ ህመሜን ምሸሽግ በሽተኛ ሰው ነኝ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እንደ ባለሽቶዋ መግደላዊት ማርያም
አንተ ባረፍክበት ማንም ባይጠራትም
ከእግሮችህ ስር ወድቃ ሽቶዋን አፍስሳ
በእንባዋ አጥባ በፀጉራ አብሳ
ከኃጢያት እስራት ስትፈልግ መላቀቅ
በንሰሃ ልንቦናዋ ምህረትን ስጠይቅ
እንደ ሰዎች ሳይሆን ልቧን ተመልክተክ
ዳግም እንዳበድዪ ብለህ እንደማርካትክ
አይደለሁም እኔ ከእግር ስር የምወድቅ
ሽቶን የማላፈስ እንባዬም ነው ደረቅ
ለታይታ የምኖር ሰዎች ምን ይሉኛል ምል
በኃጥያት ቆሽሼ ንጹህ ሰው ስመስል
የምህረት ቀኔን በከንቱ ማሳልፍ
ልበ ደንዳና ነኝ ምግባሬም የሰንፍ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ቀድመህ እንደነገርከው ለሐዋርያው ጴጥሮስ
ሥስቴ እንደሚክድህ ፍርሃት በልቡ ሲነግስ
አላቀውም ብሎ ዶሮ እስኪጮህ ድረስ
የንሰሃው ዶሮ ለጸጸት ሲያነቃው
ፊትህን አዙረህ በትዝብት ስታየው
መበደሉን ገብቶት ህሊናውን ሊወቅስ
የንሰሀን እንባ ከአይኖቹ ቢያፈስ
ምህረትን ሲሻ መጸጸቱን አይተክ
በደሉን እረስተክ ንስሀውን ተቀበልክ
እኔ ግን ደካማው በጊዜዬ ያልነቃው
ኃጥያቴን እያወኩ ንስሃ ያልገባው
የንሰሃው ዶሮ ሰልሶ ቢጮህም
ፊትህም ወደኔ በምህረት ቢዞርም
ኅሊናዬ ገብቶት ልቤ አልደነገጠም
የንስሃም እንባም ከዐይኖቼ አሎጣም
።።።።።።።።።።።።።።።፡።፡።።።።።።።።
እናም ጌታዬ ሆይ እኔ ምለምንክ
በኃጥያት ላደፍኩኝ እንዲሆነኝ ምህረትክ
በበደል ዳክሬ ቆሽሻለውና
ሆሳዕና ጌታ ፈጥነህ ወደኔና
ደንዳናውን ልቤን እንድታለሰልሰው
የልቤን መዝጊያ በር በፍቅርህ ስበረው
በኃጥያት ሸክም የዛለ አካሌን
ጉልበቴ ሆነከኝ ልስበረው ቀንበሬን
እንደ መጻጉ አልጋን ባልሸከም
የኃጥያት እግሬ ነጽቶ በንጽሐ እድቆም
ከኃጥያት ልንፃ በፍቅርህ እጠበኝ
ከበረዶም ይልቅ በምህረትህ አንፃኝ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
                ገጣሚ፦ በላይ ኃ/ሚካኤል

@ortodoxtewahedo
#ፀሎተ ሀሙስ

#ሀሙስ ምሽት ጌታችን ያደረገልን ትህትና ዮሐንስ 13

እግራቸውንም አጥቦ ልብሱንም አንሥቶ ዳግመኛ ተቀመጠ
እንዲህም አላቸው፦ ያደረግሁላችሁን ታስተውላላችሁን?
እናንተ መምህርና ጌታ ትሉኛላችሁ እንዲሁ ነኝና መልካም
ትላላችሁ።

እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ
እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ
ይገባችኋል።

እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ
ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና።

እውነት እውነት እላችኋለሁ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም።
መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም። 17 ይህን ብታውቁ
ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።
ስለ ሁላችሁ አልናገርም እኔ የመረጥኋቸውን አውቃለሁ
ነገር ግን መጽሐፍ፦ እንጀራዬን የሚበላ በእኔ ላይ ተረከዙን
አነሣብኝ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።

በሆነ ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ታምኑ ዘንድ ከአሁን ጀምሬ
አስቀድሞ ሳይሆን እነግራችኋለሁ።

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር በመጀመሪያነት ያጋሩት፦
በሰሞነ ህማማት የሚገኙ እለታትና ስያሚያቸው ........እለተ ሀሙስ -በዚህ እለት ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም ሰው ፍፁም አምላክ መሆኑን ለመግለፅና ለአርያነት ፀሀፍት ፈሪሳውያን የአይሁድ ካህናት መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲፀልይ በማደሩ ምክንያት ፀሎተ ሀሙስ በመባል ይታወቃል ፡፡

ትህትና ፍቅር መታዘዝ እንድሁም የአገልግሎትም ትርጉም
ለማስረዳትና ለማስገንዘብ እርሱ ጌታ አምላክ ሆኖ ሳለ ዝቅ ብሎ የደቀመዛሙርቱን እግር በማጠቡ ህፅበተ እግር በመባልም እንደሚጠራም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይናገራሉ ፡፡

ሀዋርያው ቅዱስ ዮሀንስም እግራቸውን አጥቦ ልብሱንም አንስቶ ዳግመኛ ተቀመጠ እንድህም አላቸው ያደረኩላችሁን
ታስተውላላችሁን እንግድህ ጌታ መምህር ስሆን እግራችሁን
ካጠብሁ እናንተ ደግሞ ለታናናሾቻችሁ እንድሁ ታደርጉ ዘንድ ይገባችኀል ሲል ተናግራል፡፡ ይኸውም ዮሀንስ ወንጌል 13 ፣12
- 20 በዝርዝር ይገኛል ፡፡

ይህ ለእናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ስጋየ ነው እንካችሁ
ብሉ ይህ ፅዋ ለእናንተ የሚፈሰው የሀዲስ ኪዳን ደሜ ነው ከእርሱ ጠጡ በማለት ሚስጥረ ቁርባንን የመሰረተበት ወይንም
እራሱ ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ሚስጥረ ቁርባንን የጀመረበት እለት በመሆኑ የሚስጥር ቀን በመባል ይጠራል ፡፡

ይኸውም የሰው ልጆች ስጋውንና ደሙን ተቀብለው ከእርሱ ጋራ
አንድነትንና ህብረትን እንድኖረን ጥንተ ጠላት ዳቢሎስን ድል
ነስተን ሰማያዊዩን እርስት እንድንወርስ ሊያደርግ ነው፡፡ ይህም በማቴወስ 26 ፣ 26 - 29 በዝርዝር ይገኛል ፡፡

አይሁድ ጌታችንን ለመያዝ በእነርሱ ጥበብና ፍላጎት ቀስ ብለው
መጥተው የያዙበት ስለሆነ በዚህ እለት በለ ሆሳስ ወይም ብዙ
የጩኸት ድምፅ ሳይሰማ የቅዳሴ ስርአት ይፈፀማል ፡፡

ስለሆነም መላው ህዝበ ክርስቲያን በዚህ የህፅበተ ሚስጥር የፀሎት እለት በሆነው በዚህ እለት በንስሀ ታጥበው የጌታን ስጋና ደሙን እንድቀበሉ ቤተ ክርስቲያን በአፅኖት ታስተምራለች ፡፡

እኛም በንስሀ ታጥበን ወደ አምላካችን ቀርበን ስጋወ ደሙን
ልንቀበል ይገባናል የጌታችን ቸርነት ፍቅሩ የእመ አምላክ
የንፅሒተ ንፁሀን የድንግል ማርያም ምልጃ የመላክት ጥበቃ
የሠማአታት ፀጋ በረከታቸው በሁላችን ላይ ይደርብን አሜን
አሜን አሜን !!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

http://www.tg-me.com/ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ/com.ortodoxtewahedo
2024/05/02 06:39:54
Back to Top
HTML Embed Code: